1/7
Holy Pictures of EOTCቅዱሳን ስዕላት screenshot 0
Holy Pictures of EOTCቅዱሳን ስዕላት screenshot 1
Holy Pictures of EOTCቅዱሳን ስዕላት screenshot 2
Holy Pictures of EOTCቅዱሳን ስዕላት screenshot 3
Holy Pictures of EOTCቅዱሳን ስዕላት screenshot 4
Holy Pictures of EOTCቅዱሳን ስዕላት screenshot 5
Holy Pictures of EOTCቅዱሳን ስዕላት screenshot 6
Holy Pictures of EOTCቅዱሳን ስዕላት Icon

Holy Pictures of EOTCቅዱሳን ስዕላት

Samuel Minale
Trustable Ranking IconAffidabile
1K+Download
54.5MBDimensione
Android Version Icon5.1+
Versione Android
4.5.1(13-02-2024)Ultima versione
-
(0 Recensioni)
Age ratingPEGI-3
Scarica
InformazioniRecensioniVersioniInformazioni
1/7

Descrizione di Holy Pictures of EOTCቅዱሳን ስዕላት

Questa APP contiene più di 400 diverse immagini sacre della chiesa ortodossa etiope di Tewahedo Santi santi, angeli santi, santi padri, sante madri e immagini sacre di Dio con un elenco di giorni santi annuali mensili che vengono celebrati nella chiesa ortodossa di Tewahedo e infine il l'app contiene un elenco di nomi biblici e le loro meningi.


Si prega di notare che le immagini sacre che si trovano in questa app non sono le uniche che ci sono molti santi che non sono inclusi in questa APP.


ከ መተግበሪያ ውስጥ ከ 400 በላይ የቅዱሳን ስዕላትን በማንኛውም ጊዜ ማግኘት እንዲችሉ ካለ ኢንተርኔት እንዲሰራ በመተግበሪያው ውስጥ ስእላቱ እንዲካተቱ ተደርጎዋል ፡፡

ከቅዱሳኑ በረከት ረድኤት ይደርብን

አሜን !!!


ከዚህ በታች ያለው አቡነ ገብርኤል በ 1990 ካሳተሙት “ክብረ ቅዱሳን» ከሚለው መጻሕፍ የተወሰደ ነው


የጥንቱና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የሚከተል ክርስቲያን ሁሉ ከቅዱሳት ሥዕሎች ሁለት ዐበይት ጥቅሞችን ያገኛል ይኽውም ትምህርትና ረድኤት ናቸው። ይልቁንም ዓለም ከመፈጠሩ በፊት የነበረው ቃለ እግዚአብሔር (አካላዊ ቃል) በኋለኛው ዘመን ሰውን ለማዳን ወደዚህ ዓለም መጥቶ ከቅድስት ድንግል ማርያም በድንግልና ተፀንሶ ከሥጋዋ ሥጋን ፣ ከነፍስዋ ነፍስን ነስቶ ከኃጢአት ብቻ በቀር ፍጹም ሰው ሆኖ በድንግልና የተወለደውና ተሰቅሎ በሞቱ ዓለሙን ማዳኑን በሥዕል ገልጾ ማቅረብ መስበክ ፤ ማስተማር ነው። በዚህም መሠረት የጌታችንን የልደቱን ታሪክ ፣ የጥምቀቱን ታሪክ ፣ የስቅለቱን ታሪክ ፣ የትንሣኤውንና የዕርገቱን ታሪክ በሥዕል ነድፎ ለምእመናን ማቅረብ ማለት የጌታችንን ወንጌለ መንግሥት መስበክና ማስተማር ማለት ነው ምክንያቱም ሥዕል ራሱበጉልህ የተጻፈ ጽሑፍ ማለት ነውና። ጌታችን ተወለደ ፣ ተጠመቀ ፣ ተሰቀለ ፣ ሞተ ፣ ከሙታን ተለይቶተነሣ… የሚለው የወንጌሉ ታሪክ በሥዕል ማቅረብ ማለት ታሪኩን በጉልህ ጽፎ ማቅረብ ማለት ነው።

ሐዋርያው ​​ቅዱስ ጳውሎስ ለገላትያ ክርስቲያኖች ተግሳጽ ሲጽፍ «የማታስተውሉ የገላትያ ሰዎች ሆይ ፤ በዓይናችሁ ፊት ኢየሱስ እንደተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ ነበር »ያለው ኢየሱስና ታሪኩን በሚገባ አውቀውትና ከልብም ተረድተውት እንደ ነበር ለመግለጽ ነው (ገላ .3 ፤ 1-2)


ስለዚህ ከላይ እንደተገለጸው ቅዱሳት ሥዕሎች በመመልከትና ልብ ብሎ በማንበብ (በማስተዋል) ታሪኩን በሚገባ ማወቅና መረዳት ስለሚቻል ፤ ስለዚህ በቤተ ክርስቲያን የሚገኙ ሥዕሎች የክርስትና ሃይማኖት አስተማሪዎችና አስረጂዎች መሆናቸውን መገንዘብ ተገቢ ነው።


ሁለተኛው ጥቅም ከቅዱሳት ሥዕሎች የሚገኘው ሌላው ዐቢይ ጥቅም ደግሞ ረድኤት (ርዳታ) ነው።


ኢየሱስ ክርስቶስ በነበረበት በጣም ቅርብ የነበሩት የጥንት ክርስቲያኖች በጌታችን ሥዕል ፣ በቅድስት ድንግል ሥዕልና በቅዱሳን ሥዕሎች ይማፀኑ እንደ ነበር የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ይመሰክራል። በዘመናችን ተቆፍረው የተገኙ የጥንት አብያተ ክርስቲያናት ፍርስራሶችም በሥዕላተ ቅዱሳን መማፀን ጥንታዊ ትውፊት (ሥርዓት) እንደሆነ ያመለክታሉ ታሪክን መካድ ደግሞ አያትና ቅድመ አያትን መካድ ማለት ነው። ስለ ሥዕል ክብር የቤተ ክርስቲያን ትውፊታዊ ታሪክ ምስክር ነው። የታወቀው ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊ አውሳብዮስ ኤጲስ ቆጶስዘቂሳርያ ስለ ጌታ ሥዕል አጀማመርና አመጣጥ ጽፎ ያቀረበውን ብፁእ አባ ጎርጎርዮስ ሊቀ ጳጳስ ዘሸዋበመጽሐፋቸው ጠቅሰውታል። አኛም የጥቅሱን ፍሬ ነገር ቀጥለን ጠቅሰነዋል።


«ንጉሥ ዐብጋር በዑር (ኤዴሣ ከተማ የአገሩ ንጉሥ በመሆን ጌታችን በነበረበት ዘመን ይኖር ነበረ ፤ ስሙም (ልዑካን) ይባል ነበር። ዐብጋር ማለት በከለዳውያን ቋንቋ ቄሣር ማለት ነው። ዐብጋር በዚያ ዘመን በጠና ታሞ ነበር ፤ የጌታችንን ተአምራት በዝና ሰምቶ ይፈውሰው ላከለት ፤ ጽፎ ለጌታችን ፤ ፤ ደብዳቤውን ከመልእክተኛው እጅ ተቀብሎ ካነበበው በኋላ «ሳያየኝ ያመነኝ ዐብጋር ብፁዕ ነው» ብሎ ዐብጋርን በማመስገን በሱ ስም እንዲፈውሰው ከደቀ መዛሙርቱ መካከል አንዱን እንደሚልከለት በመግለጽ መልስ ላከለት። ነገር ግን ከጌታ ጋር ተገናኝቶ የተመለሰው የዐብጋር (ዩካማ) መልእክተኛ ሠዓሊ ስለነበር ከጌታችን ጋር ሲነጋገር ፊቱን በሥዕል ነድፎ (ሥሎ) ከደብዳቤው ጋር ይዞ ተመለሰ። ከዚያም አንደ ደረሰ ከጌታ የተላከውን ደብዳቤ ለታመመው ንጉሥ አነበበለት ፤ ሥዕሉንም አሳየው። በዚያን ጊዜ በሽተኛው ንጉሥ የጌታችንን ቃል ከደብዳቤው ሰምቶና ሥዕሉንም በዓይኑ ተመልክቶ ወዲያው ከሕመሙ እንደ ተፈወሰ ታሪኩ ያስረዳል (አባ ጎርጎርዮስ ፤ የኢ ኦ ተ ቤተ ክርስቲያንታሪክ 1974 ገጽ 119 120)።


ይኽው አውሳብዮስ ስለ ጌታችን ሥዕል የሰጠው ምስክርነት እንዲህ የሚል ነው «ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ ዓርብ ደሙን እያንጠፈጠፈ መስቀሉን ተሸክሞ ወደ ጎልጎታ በሚጓዝበት ወቅት እያለቀሱ ከሚከተሉት ደጋግ ሴቶች መካከል ቬሮኒካ የተባለች ደግ ሴት የራስዋን መሸፈኛ አውልቃፊቱን አንዲያድፍበት (እንዲጠርግበት ስጌታ ወረወረችለት ፤ ጌታችንም በደምና በላብ የተጠመቀውንሥዕለ ቀረ ማለት የፊቱ መልክ በሻሽዋ ላይ ታትሞ ቀረ »በማለት ከላይ የጠቀስነው የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊው አውሳብዮስ ይመሰክራል።


ስለ ቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ደግሞ ወላዲተ አምላክ በነበረችበት ክፍለ ዘመን የነበረው ሐዋርያው ​​ቅዱስ ያዕቆብ የጌታን ታሪክ (ወንጌል) ሲጽፍ ስለ ወላዲተ አምላክም ብዙ ጽፎአል። በዚህ የያዕቆብ ወንጌል (ያዕቆብ ታሪክ) በተባለው የትውፊት መጽሐፍ ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ ለመጀመሪያ ጊዜ የማርያምን ሥዕል መሃሉ ተጽፎአል።


አውሳብዮስ ኤጲስ ቆጶስ ዘቂሳርያና ሌሎችም የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፊዎች እንደ መሰከሩት የጥንትዋ ቤተ ክርስቲያን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥዕል ፣ ለወላዲተ አምላክ ፣ ለቅዱሳን መላእክት ፣ ለጻድቃንና ለሰማዕታት ሥዕሎች ከፍ ያለ ክብር እንዲደረግላቸውና የጸጋና የአክብሮት ስግደት እንዲቀርብላቸው ስታስተምር ኖራለች። ምእመናንም በቤተ ክርስቲያን ትምህርት መሠረት በሚጸልዩበት ቤተ ክርስቲያንና በቤታቸው በሚገኘው በግል ጸሎት ቤታችው የጌታችንን ፣ የቅድስት ድንግል ማርያምና ​​የቅዱሳንን ሥዕሎች በግድግዳው በመስቀልና የክብር ስግደት በማቅረብሲማፀኑባቸው ኖረዋል።


በዚሁ ሁኔታ የሥዕል ክብር በጥንትዋ ቤተ አስከ እንደ መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ድረስ ከቆየ በኋላ ሳይታሰብ በድንገት ከክርስቲያኖቹ መካከል ጥቂቶች ሰዎች የሥዕልን ክብር በመቃወም ተነሡ። በዚሁ ምክንያት በሮምና በቢዛንታይን ግዛቶች ከባድ ክርክርና ሁከት ተቀሰቀሰ። 97 ጊዜ በ 797 ዓም የምስራቅቤተ ክርስቲያን መሪዎች ጉባዔ አድርገው የቅዱሳንን ሥዕሎችማክበርና መሳም (መሳለም) እንደሚገባ ለሥዕሎቹም የአክብሮት ስግደት ማቅረብ ተገቢ መሆኑን በሰፊው አትተው ወስነዋል ...

ቀሪውን ከዌብሳይቱ ላይ ያንብብቡ

Holy Pictures of EOTCቅዱሳን ስዕላት - Versione 4.5.1

(13-02-2024)
Altre versioni
Che cosa c'è di nuovoSharing Holy Picture is now addedMore Holy Pictures AddedSome bugs fixed specially for android 5+ usersbugfix

Non ci sono ancora recensioni né valutazioni! Per essere il primo a lasciare un commento,

-
0 Reviews
5
4
3
2
1
Info Trust Icon
Ottima App garantitaQuesta applicazione ha superato il test di sicurezza per virus, malware e altri attacchi dannosi e non contiene minacce.

Holy Pictures of EOTCቅዱሳን ስዕላት - Informazioni APK

Versione APK: 4.5.1Pacchetto: sammy.saintpictures.ethiopianorthodoxtewahedochurchholypictures
Compatibilità Android: 5.1+ (Lollipop)
Sviluppatore:Samuel MinaleInformativa sulla Privacy:https://onesam55.wixsite.com/holypicturesAutorizzazioni:12
Nome: Holy Pictures of EOTCቅዱሳን ስዕላትDimensione: 54.5 MBDownload: 15Versione : 4.5.1Data di uscita: 2024-06-06 05:10:33Schermo minimo: SMALLCPU Supportate:
ID del pacchetto: sammy.saintpictures.ethiopianorthodoxtewahedochurchholypicturesFirma SHA1: 20:92:B5:A9:9B:67:15:CB:DA:D5:D3:9E:DC:EF:04:8C:90:E3:05:C9Sviluppatore (CN): Samuel MinaleOrganizzazione (O): Localizzazione (L): Paese (C): 00251Stato/città (ST):

Ultima versione di Holy Pictures of EOTCቅዱሳን ስዕላት

4.5.1Trust Icon Versions
13/2/2024
15 download54.5 MB Dimensione
Scarica

Altre versioni

4.4.1Trust Icon Versions
12/8/2020
15 download40 MB Dimensione
Scarica

App nella stessa categoria

Potrebbe piacerti anche...